Trainings

1.የአመጋገብ ፈተናዎችና ተግባራዊ መፍትሔዎች Nutrition Challenges & Practical Solutions

ይህ ስልጠና 5 ሰዓታት ያህል የሚፈጅ ሲሆን የምጀምረው ቅዳሜ ሴፕተምበር 5/2026 ከጧቱ 9AM Central Time ነው።

በምዕራባዊው ዓለም የምናገኘው ዘመናዊ የአመጋገብ ሁኔታ ለብዙ ቤተሰቦች የጤና ፈተና ሆኗል። ከመጠን በላይ ፕሮሴስ የተደረጉ ምግቦች፣ ከፍተኛ ስኳር፣ ጎጂ ቅባቶች እና ተደጋጋሚ ፈጣን ምግቦች የውፍረት፣ የስኳር በሽታ፣ የደም ግፊት፣ የልብ ሕመም እና ሌሎች ከአኗኗር ጋር የተያያዙ የጤና ችግሮችን እየጨመሩ ነው። በተለይም ልጆቻችን እና ወጣቶቻችን የሚያድጉበት የምግብ ባህል የወደፊት ጤናቸውን በእጅጉ ይጎዳል። ስለዚህ ትክክለኛ የሥነ-ምግብ እውቀት ማግኘት የምርጫ ጉዳይ ሳይሆን የቤተሰባችንን ጤና ለመጠበቅ እና ቀጣዩን ትውልድ ጤናማ ለማሳደግ አስፈላጊ ኃላፊነት ነው። በትክክለኛ እውቀት እና በተግባራዊ የአመጋገብ ልምዶች ዛሬ የምንወስደው ውሳኔ የነገውን የቤተሰባችን ጤና እና የትውልዳችንን ወደፊት ሊለውጥ ይችላል። ይህንን ስልጠና በመውሰድ ለጤናዎ፣ ለቤተሰብዎ እና ለትውልድዎ ዘላቂ ለውጥ የሚያመጣ እውቀት ያገኛሉ፤ ይህ ስልጠና የሕይወትዎን አቅጣጫ ሊቀይር የሚችል እውነተኛ ጉዞ ነው።

ለመመዝገብ ይህንን ሊንክ ይጫኑ። በቁጥር የተወሰነ ሰው ብቻ ስለምንቀበል ዛሬዉኑ ይመዝገቡ

2. የጾም ቁልፍ ጥቅሞችና ሙሉ መመሪያ: Key Benefits of Fasting & guidance

ይህ ስልጠና 5 ሰዓታት ያህል የሚፈጅ ሲሆን የምጀምረው ቅዳሜ ሴፕተምበር 19/2026 ከጧቱ 9AM Central Time ነው።

ጤናማ ምግብ መመገብ ለሰውነታችን ትልቅ ጥቅም ቢኖረውም፣ በአግባቡ መጾም ለሰውነታችን እረፍት በመስጠት የበለጠ የጤና ጥቅሞችን ሊያስገኝ ይችላል። የጾምን ትክክለኛ መመሪያ ማወቅ ከብዙ ከአኗኗር ጋር የተያያዙ የጤና ችግሮች ራስዎንና ቤተሰብዎን ለመጠበቅ ይረዳል። በዚህ ልዩ ስልጠና የጾምን ሳይንሳዊ መሠረት፣ ትክክለኛ አተገባበር፣ ጥቅሞቹ እና በአስተማማኝ ሁኔታ እንዴት መጾም እንደሚቻል በዝርዝር ይማራሉ። ይህ እውቀት ለጤናዎ፣ ለቤተሰብዎ እና ለወደፊት ትውልድዎ የሚጠቅም ዘላቂ መሠረት ይሆናል።

ለመመዝገብ ይህንን ሊንክ ይጫኑ። በቁጥር የተወሰነ ሰው ብቻ ስለምንቀበል ዛሬዉኑ ይመዝገቡ

3.የአንጀትና የአእምሮ ጤና ማስተር ክላስ: Gut & Mental Health Master Class

ይህ ስልጠና 5 ሰዓታት ያህል የሚፈጅ ሲሆን የምጀምረው ቅዳሜ October 10/ 2026 ከጧቱ 9AM Central Time ነው።

አንጀታችን ጤና በምግብ መፈጨት፣ በቫይታሚንና በማዕድናት መውሰድ፣ በበሽታ መከላከል፣ በአእምሮ ጤና፣ በስሜታዊ መረጋጋት እና በአጠቃላይ ሰውነታችን ጤና ላይ ከፍተኛ ሚና ይጫወታል። አንጀትና አእምሮ በቀጥታ የተገናኙ በመሆናቸው የአንጀት ጤና መታወክ በስሜት፣ በውጥረት፣ በጭንቀት እና በአጠቃላይ በአእምሮ ጤና ላይም ተጽዕኖ ሊያሳድር ይችላል። የአንጀት ጤና ሲበላሽ የተለያዩ የጤና ችግሮች ሊከሰቱ ይችላሉ። ከዚህ በፊት አንቲባዮቲክ ወስደው ያውቃሉ? ከአንቲባዮቲክ ሕክምና በኋላ የአንጀት ጤናን ለመደገፍ የሚረዱ ጠቃሚ ባክቴሪያዎችን እንዴት እንደሚደግፉ ያውቃሉ? ተደጋጋሚ የሆድ ምቾት ማጣት፣ ጋዝ፣ የሆድ መነፋት (Bloating)፣ አለርጂ ወይም ከራስ-መከላከያ ሥርዓት (Autoimmune) ጋር የተያያዙ ችግሮች እንዳያጋጥሙን ምን ማድረግ እንዳለብን ያውቃሉ? በዚህ ልዩ ስልጠና የአንጀትን ጤና እንዴት ማሻሻልና መጠበቅ እንደሚቻል፣ የአንጀትና የአእምሮ ጤና ትስስር፣ የጠቃሚ የምግብ ምርጫዎች፣ የአኗኗር ልምዶች፣ እንዲሁም በየቀኑ ሊተገበሩ የሚችሉ ተግባራዊ መፍትሔዎችን በሳይንሳዊ መሠረት ይማራሉ። ይህ ስልጠና የራስዎን፣ የቤተሰብዎን እና የትውልድዎን ጤና ለማሻሻል የሚረዳ ጠቃሚ እውቀት ያስታጥቃችኋል።

ለመመዝገብ ይህንን ሊንክ ይጫኑ። በቁጥር የተወሰነ ሰው ብቻ ስለምንቀበል ዛሬዉኑ ይመዝገቡ

4.የስኳር በሽታ፣ ውፍረት፣ ከፍተኛ ኮሌስትሮልና የደም ግፊት መንስኤዎቻቸውና ተግባራዊ መፍትሔዎች

ይህ ስልጠና 6 ሰዓታት ያህል የሚፈጅ ሲሆን የምጀምረው ቅዳሜ October 31/ 2026 ከጧቱ 9AM Central Time ነው።

የስኳር በሽታ፣ ውፍረት፣ ከፍተኛ ኮሌስትሮልና የደም ግፊት ዛሬ በዓለም ዙሪያ ከፍተኛ የጤና ፈተና ሆነዋል። እነዚህ የሜታቦሊክ በሽታዎች በየቤቱ እየገቡ ማንኛውንም ቤተሰብ ሊነኩ ይችላሉ። የሚያሳዝነው ብዙ ሰዎች በሽታዎቹ እንዴት እንደሚጀምሩና እንዴት ሊከላከሉ እንደሚችሉ በቂ እውቀት የላቸውም። በዚህ ስልጠና የእነዚህን በሽታዎች መንስኤዎች፣ የአደጋ ምክንያቶች እና በሳይንስ የተደገፉ ተግባራዊ የአኗኗርና የአመጋገብ መፍትሔዎችን ይማራሉ። ዛሬ የሚያገኙት እውቀት የራስዎን፣ የቤተሰብዎን እና የወደፊት ትውልድዎን ጤና ለመጠበቅ ወሳኝ መሠረት ይሆናል። ይህ ስልጠና በሽታው ላለባቸው ብቻ አይደለም። ዛሬ ጤናማ ቢሆኑም ነገ ከእነዚህ በሽታዎች ራስዎንና ቤተሰብዎን ለመጠበቅ የሚያስፈልግዎትን እውቀት ያገኛሉ። ከብዙ ጊዜ ውድ ሕክምናን ከመፈለግ ይልቅ ትክክለኛውን እውቀት በጊዜው ማግኘት ለጤናዎ የሚያደርጉት ከፍተኛ ኢንቨስትመንት ነው። ዛሬ የሚማሩት እውቀት የነገውን ጤናዎን ሊወስን ይችላል። ለራስዎ፣ ለቤተሰብዎ እና ለቀጣዩ ትውልድ የሚጠቅም ይህን ልዩ ስልጠና አያምልጥዎ።

ለመመዝገብ ይህንን ሊንክ ይጫኑ። በቁጥር የተወሰነ ሰው ብቻ ስለምንቀበል ዛሬዉኑ ይመዝገቡ

Connect (ተጨማሪ መረጃ ከፈለጉ)

Reach out for support or questions anytime

Emai l:

Text us: +1 (512)-501-0734 (አስቀድሞ የሚፈልጉትን አገልግሎት Text ያድርጉልን)

© 2025. All rights reserved.