HOPE
ም ግ ብ መ ድ ሃ ኒ ት ነ ው!
በግል አንድ-ለአንድ፣ እንዲሁም አባት፣ አናትና፣ ልጅን ጨምሮ ለቤተሰብ የተዘጋጀ ምክርና ስልጠና እንሰጣለን።
Personalized nutrition coaching tailored to you
Simple wellness habits for everyday balance
Motivation and tools to unlock your potential




Welcome to Azebina Show
የአዜቢና ሾው ላለፉት ለአሰርት እመታት አመጋገባችንንና የኑሮ ዘይቤን በመለወጥ በጤና መኖር እንደሚቻል ህብረተስባችንን እያስተማረና እየረዳ የሚገኝ በብዙዎች የተመሰከረለት ፕላትፎርም ነው።
በመቶዎችና በሺዎች የሚቆጠሩ ግለሰቦች በምንሰጠው መረጃ ከሞት አፋፍ ድነዋል። የምናበረክተው እርዳታ በጣም ቀላል፣ ጊዜና ወጪ የማይጠይቅ ለሰው ዘር በሙሉ የሚስማማ ነው። በጤና እክል ተስፋ የቆረጣችሁና ስጋት ዉስጥ የገባችሁ "ምግብ መድሃኒት" መሆኑን በተግባር የሚታዩበት ቦታ ነው።
ብዙዎቻችን እርዳታ የምንፈልገው ከታመምንና አልጋ ላይ ከወደቅን በኋላ መሆኑን ተገንዝበን፤ የከፋ ነገር በራችንን ከማንኳኳቱ በፊት ምን ማድረግ እንዳለብን መረጃ እንሰጣላን። ዛሬ ያለን ጤና ለነገው ዋስትና እይሆንምና። ምግብን እንደመድሃኒት መጠቀም መድሃኒትን እንደምግብ ከመዉሰድ ይጠብቀናል!
Practical Guidance for Your Health and Wellness Journey!


1.2 M+
5,000+
በግል የተረዱ ሰዎች ቁጥር
ይህ መረጃ የየደረሳቸው ሰዎች ብዛት
Our Services
Practical guidance to boost your health and mindset daily.
Nutrition Coaching
Personalized plans to nourish your body effectively. አዜቢና ሾው ከምግብ አመራረጥ አንስቶ እስከ አበሳስል፣ አልፎም ማን ምን መመገብ እንዳለበት፤ መቼና በምን አይነት ሁኔታ መብላት እንዳለበት በሳይንስና በምርምር የተደግፉ መረጃዎችን ለህብረተስባችን በመስጠት ላይ ይገኛል።
Wellness Insights
Science-backed tips for balanced living every day! ነገር ሁሉ በምግብ አይፈታም። የፈለገዉን ይህል በልተን እንቅስቃሴ ካላደረግን፤ ኳሊቲ እንቅልፍ ካልተኛን፣ ጭንቀትና ድባተን ካልተቆጣጠርን፣ የቤታችንና የዉስጣችንን ሰላም ካልጠበቅን ሰው ሙሉ ጤና አለው ማለት አይቻልም።
አዜቢና ሾው ከምግብ ጎን ለጎን ለጤናዎ የሚረዱ በሳይንስና በልምድ ተሞክረው ጉልህ ዉጤት ያስገኙትን ልምምምዶች ይዞላችሁ ቀርቧል። ጤናዎትን ያማከለ እንቅሰቃሴ፣ አተነፋፈስ፣ ለእንቅልፍና ለጭንቀት መቆጣጠሪያ የሚረዳዎትን መላ ይጠቁሞታል።
Personal Growth
Simple strategies to create lasting positive! routines. የጀመራችሁትን የጤና ግብ ለመምታት በጋር እንሰራለን። በየቀኑ ያሉበትን ሁኔታ በቅርበት እንከታተለለን፣ የመጣዉን አሉታዊና አዎንታዊ ዉጤት በአንድነት እንገመግማለን። የተሻለ ሞያዊ አቅጣጫ እንጠቁማለን፤ ተለዋጭ መፍትሄ እንሰጣለን።
Join Us
ከሃገር ዉጪ ያሉ ኢትዮጵያዉያንና ኤርትራዉያን በምዕራቡ ዓለም ስርዓተ-ምግብ ዉስጥ ማድረግ ያለባቸዉን ጥንቃቄ፣ የምዕራባዉያን አመጋገብና life style በጤናችን ላይ የሚያሳድረዉን ተፅዕኖ በስፋት እናስተምራለን። የኪቶጀኒክ ዳይትና ካርኒቮር ዳይት ተብሎ የሚታወቁትን የዳይትና ላይፍ ስታይል ዓይነቶች በመጠቀም በሺዎች የሚቆጠሩ ህጻናትንና አዋቂዎችን በመርዳት ላይ እንገኛለን። የአዜቢናን ቤተሰብ ለመቀላቀልና አንድ-ለአንድ እርዳታ ከፈለጉ ስልካችንና ኢሜላችንን ከዚህ በታች ያገኛሉ። ደውሉልን።
አዜቢናን ተከታትዬ ለ13 አመታት ሲስቃይበት ከነበረው ስኳር በሽታዬ ሶስት ወር ባልሞላ ጊዜ ነጻ ወጥቻለሁ። ህይወቴ ተቀየረ፣ ወደ ኑሮዬ አሁን ተመልስኩ። እግዚአብሄር ዘመንሽን ይባርክ
ቤቲ

ለስድስት አመት በሙሉ ከሰው ጋር አልገናኝም ነበር፤ ቆዳዬና ፊቴ ቆስሎ አዲስ አበባ ኣለርት ሆስፒታ ገንዘቤን ጭርሼ ባዶ እጄን ባለሁበት ነበር አዜቢናን ተከታትዬ ነጻ የወጣሁት። አላህ ይባርክሽ ሌላ ምን እላለሁ
ሙና

★★★★★
★★★★★
Connect (ተጨማሪ መረጃ ከፈለጉ)
Reach out for support or questions anytime
Emai l:
Call: +1 (512)-553-9080 (please text us first)
© 2025. All rights reserved.
